Abebe Kebie
Consultant

ጤና ይስጥልኝ!

አበበ ከቤ ሁነኛው እባላለሁ፡፡ ሰርቲፋይድ የማኔጅመንት (ስራ አመራር) አማካሪ፣ አሰልጣኝና ተመራማሪ ነኝ፡፡ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለበርካታ አመታት በድህረ ምርቃና ቅድመ ምረቃ ደረጃ በማስተማር ላይ እገኛለሁ፡፡ እንዲሁም በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ በንግድ ድርጅትቶች ውስጥ በአማካሪነትና በአሰልጣኝነት እሰራለሁ፡፡ በግሌ የአንኳር ማኔጅመንት ሶሊሽንስ የስልጠና እና ማማከር አገልግሎት መስራችና ስራ አስኪያጅ ነኝ።

በሽዎች ለሚቆጠሩ ግለሰቦች እና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ድርጅቶች በገበያ ስራ አመራር፣ስትራቴጅክ ስራ አመራር፣ በሽያጭ ስራ፣ በደንበኞች አገልግሎት መርሆች፣ ኢንተርፕርነርሽፕ ፣ ፕሮጀክት አስተዳደርና አመራረር፣ የለውጥ አስተዳደርና ድርጅታዊ ኢኖቬሽን፣ ወዘተ… ዙሪያ በርከት ያሉ ስልጠናዎችንና የማማከር ስራዎችን ሰርቻለሁ። በመሆኑም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ‘የተወሰነ’ ግንዛቤ አለኝ ብየ አምናለሁ። በአሁኑ ስዓት ከስልጠናና የማማከር አገልግሎት በተጨማሪ የበለጠ ተደራሽ ለመሆን በሂደቱም ያለኝን ልምድና ዕውቀት በማካፈል እኔም በሂደቱ ለመማርና ልምዴንና እውቀቴን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ መፅሀፎች በመፃፍ እንዲሁም በይነ መረብ እና የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሃሳቦችን በማጋራት ላይ እገኛለሁ።

በስራ አመራር፣ስትራቴጅክ ስራ አመራር፣ በሽያጭ ስራ እና የገበያ ስራ አመራር፣ በደንበኞች አገልግሎት መርሆች፣ ኢንተርፕርነርሽፕ እና ስራ ፈጠራ ፣ ፕሮጀክት አስተዳደርና አመራረር፣ የለውጥ አስተዳደርና ድርጅታዊ ኢኖቬሽን፣ የስብዕና ግንባታና ብልፅግና፣ ወዘተ…ዙሪያ አብሮ ለመስራት ይወዳጁኝ፣ ይከተሉኝ፣ ይፃፉልኝ።

Subscribe to our Newsletter

Stay updated with the latest news, articles, and resources, sent to your inbox weekly.